በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሰጥ አገባ ክርክር፥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የት ናቸው?


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የጤና እክል ተከትሎ፥ ከ45 ቀናት በላይ ያሉበት ቦታና የጤና ሁኔታ በውልና በይፋ ያለመረጋገጥ ዛሬም የተለያዩ ወገኖችን እያወዛገበና እያነጋገረ ነው።

የብሪታንያው ጋዜጣ Financial Times በዛሬው እትሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአፍሪካ ኅብረት በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ጉዳዮች ላይ እያካሄደ ባለው ድርድር ከዋናው አደራዳሪ ደቡብ አፍሪቃው የቀድሞ ፕሬዝዳንት Thabo Mbeki ጋር ሲነጋገሩ እንደነበር ዘግቧል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ወደ ሥራቸው የሚመለሱ መሆናቸውን የኮምዩኒኬሽን ሚንስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ከአንድ በአውስትራሊያ ከሚገኝ የአካባቢ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

«እሰጥ አገባ፤» የክርክር ፕሮግራም በርዕሱ ዙሪያ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ያስተላለፈውን የዚህን የሁለት ወገን ክርክር ከዚህ ያድምጡ፤

ክፍል አንድ፤

ክፍል ሁለት፤

XS
SM
MD
LG