በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክርክር፥ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታና የትነት አሁንም እያነጋገረ ነው


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የጤና እክል ተከትሎ፥ ከ45 ቀናት በላይ ያሉበት ቦታና የጤና ሁኔታ በይፋና በውል ያለመረጋገጥ ዛሬም የተለያዩ ወገኖችን በማወዛገብና በማነጋገር ላይ ይገኛል።

ሰሞንኛውን፥ «በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ ናቸው፤» ከሚለው ያሉበትን ይፋ ካላደረገው የመንግስቱ መግለጫ ጨምሮ፤ «የለም፥ በጠና ታመዋልና በዚሁ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፤» እስከሚሉት ድረስ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጤንነት የተመለከተ ርዕስ አሁንም ይበልጥ እያወዛገበ ነው።

ሁኔታውን መነሻ ያደረገው እሰጥ አገባ፥ የክርክር ፕሮግራም የሁለቱን ወገኖች ክርክር አስተናግዷል።

የክርክሩን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG