በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቅርቡ ለደረሱት አብያተ ክርስትያናት ቃጠሎ ከጊዜያዊው መነሻዎች ባሻገር ለዓመታት የቆዩ የተሳሳቱ ምክኒያቶች አሉ ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች አመለከቱ


ከሳምንት በፊት በጂማ ዞን አሰንዳቦ ከተማ ተጀምሮ ወደ ጭሮ አፈታ ኦሞ ናዳ እንዲሁም ወደ ሌሎች ወረዳዎች የተዛመተዉ የቤተ ክርስቲያኖችና የግል ቤቶች መቃጠልና የሰዎች መፈናቀል ነዉ፤ ለዛሬዉ ጥያቄዎ መልስ ርእስ መነሻ የሆነን። ሆኖም ስለዚህ ክስተት ስንዘግብ ካሁን በፊት በጉራጌ ዞን ዘጠኝ መስኪዶች እንደተቃጠሉ አንድ ሌላ መስጊድ በአዲስ አበባም ተቀጥሎ እንደነበር ከአድማጮቻችን በብዛት መረጃዎች እየደረሱን ነዉ።

ከዚህ ቀደምም በሌሎች የክርስቲያን እምነት ዘርፎች መሃል እንዲሁም በሙስሊምና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መካከል ግጭቶች እንደነበሩ፥ በአደጋዎቹም ህይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ አይዘነጋም። ይህ በአገሪቱ ያልተለመደና መጥፎ አዝማሚያ እንዴት ሊቆም እንደሚችል እንዲያዋዩንና ለአድማጮችም ጥያቄ መልስ ይሰጡ ዘንድ ሁለት የሃይማኖት መሪዎችን ጋብዘናል።

የተለያዩ እምነቶችን የሚከተል ኅዝብ ለዘመናት በፍቅርና በመከባበር በጉርልትናና በወዳጅነት ሲኖር እንደቆየው ሁሉ፥ በአሁኑ ወቅት የሚታዩት ግጭቶች እንዳይቀጥሉ ለማድረግና እንደ ቀድሞው በሰላማዊ መንገድ ኑሮዉን መምራት ይችል ዘንድ ከቤተ እምነት መሪዎች ምን ይጠበቃል? ከመንግስትስ?

ለዝርዝሩ፥ የአድማጮችን ጥያቄዎች በሥፋት የተስተናገዱበትን የሳምንቱን ለ«ጥያቄዎ መልስ፤» ዝግጅት ያዳምጡ፤

XS
SM
MD
LG