የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት አማራጭ ያላቸውን የተለያዩ አሠራሮች በተግባር እየፈተሸ ነው። በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀውና ለአምስት ቀናት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዶ ባለፈው ቅዳሜ በተጠናቀቀው የክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በየዘርፉ ተስፋ የተጣለባቸውን አትሌቶች ለማየት መቻሉን ከምንጮቻችን ተረድተናል።
በውድድሩ መዝጊያ ላይ ከተካሄዱት የሩጫ ውድድሮች በአጭር ርቀት 400 ሜትር የዱላ ቅብብል ከጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ተቋም የተገኙት አትሌቶች የሚቀመሱ አlሆኑም። በአንደኝነት አጠናቀዋል።
በሌላ አትሌቲክስ ዜና፥ ከ 51 ዓመት በፊት በሮም ኦሊምፒክ ለሀገሩና ለአፍሪቃ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ባስገኘው በሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የተዘጋጀ የአሥር ኪሎ ሜትር የጐዳና ሩጫ ውድድር ትላንት በመሃል አዲስ አበባ ተካሂዷል።
በእግር ኳስ በሣምንቱ ማብቂያ ቅዳሜና እሁድ የአፍሪቃና የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ እንዲሁም የተወሰኑ የወዳጅነት ግጥሚያዎች ተካሂደዋል።
ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።