በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሰዎች ታሰሩ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሃሰተኛ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሚማሩ በማስመሰል የተመዘገቡ 138 ሰዎችን መንግሥቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አንድ ፌደራል ባለሥልጣን አስታወቁ። ባለሥልጣኑ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተጨማሪ ሰዎችም ሰሞኑን እንደሚያዙ አረጋግጠዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሃሰተኛ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሚማሩ በማስመሰል የተመዘገቡ 138 ሰዎችን መንግሥቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አንድ ፌደራል ባለሥልጣን አስታወቁ።

ባለሥልጣኑ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተጨማሪ ሰዎችም ሰሞኑን እንደሚያዙ አረጋግጠዋል።

የማጭበርበር አድራጎት ፈፅሟል የተባለው የይስሙላ ዩኒቨርሲቲ መቼም ቢሆን ዲግሪ እንደማያገኙ እያወቁ በራሳቸው ፍቃድ የሚመዘገቡና የሚከፍሉ ሰዎችን እያግባባ የተማሪ ቪዛ እንደሚያሰጣቸው ከትናንት በስተያ ረቡዕ ችሎት ላይ የቀረበ የክሥ ዶሴ አመልክቷል።

ዩኒቨርሲቲ ነኝ የሚለው የማጭበርበርያው ቀለበት ለእነዚያ ምንም ትምህርት ለማይከታተሉ ሰዎች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ “የትምህርት ልምምድ ሥልጠና” ወይም ሲፒቲ የሚባለውን የቪዛ መርኃግብር እንዲያገኙና ሥራ ላይ መሠማራት እንዲችሉ ሲያደርግ መቆየቱን ክሡ ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ሠራተኞች ናቸው የተባሉ ሰዎች ከዲትሮይት ሚሺጋን ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ስም “ፋሚንግተን ዩኒቨርሲቲ” የሚባል ሃሰተኛ ተቋም የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ መክፈታቸውን ካስታወቁ በኋላ ከስድስት መቶ በላይ የውጭ ሃገሮች ዜጎች መመዝገባቸውን የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ይህ የማጭበርበሪያ ተቋም በአካል የሚገኝበት ቦታም ሆነ የትምህርት ክፍሎች የሌሉትና በማንኛውም ሕጋዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተመዘገበም እንዳልሆነ መንግሥቱ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG