በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል እና ጋምቤላ ክልል “ህገወጥ ተግባር ሊፈፅሙ ነበር” የተባሉ ግለሰቦች ተያዙ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "መንግሥት የለም በማለት ህገወጥ ተግባርን ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 37 ግለሰቦችን ይዣለሁ" ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

"ሠላሳ የሚሆኑ የህወሓት አባላትና ባለሃብቶች ሲሆኑ ሰባቱ ደግሞ የኦነግ ሸኔ አባላት ናቸው" ብሏል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱላዚዝ መሃመድ።

በተመሳሳይ ሁኔታ በጋምቤላ ክልልም ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጋጨት አሲረው ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የተጠረጠሩ የህወሃትና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች ናቸው ያላቸው 19 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቤንሻንጉል እና ጋምቤላ ክልል “ህገወጥ ተግባር ሊፈፅሙ ነበር” የተባሉ ግለሰቦች ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:48 0:00


XS
SM
MD
LG