መቀሌ —
ዓረና ትግራይ በቅርቡ አራተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
በዚህም በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካዊ ሳይንስ ምሁርና መምህር አቶ አብርሃ ደስታን በሊቀመንበርነት መርጧል፡፡
ዓረና በጉባኤው ወቅት የድርጅቱ የፖለተካ ኣቅጣጫ በሚመለከት በዝርዝር እንደተወያየ ተገልጿል፤ እንዲሁም በወልቃይት ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል የመፍትሔ አቅጣጫም ተጠቁሟል፡፡
ዓረና ከኤርትራ ጋር ስላለው ግኑኝነት እንዴት መፈታት እንዳለበትም ተወያይቶበታል፡፡
ግርማይ ገብሩ አዲሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አብርሃ ደስታን በዚሁና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አነጋግሯል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ