በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓሪስ ባቡር ጣቢያ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ቦምብ ተገኘ


ፓሪስ በሚገኘው ጋሬ ዱ ኖርድ ጣቢያ ሐዲድ አቅራቢያ የሁለተኛ የዓለም ጦርነት ቦምብ በመገኘቱ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተሳፋሪዎች ባቡር ለመሳፈር ሲጠባበቁ።
ፓሪስ በሚገኘው ጋሬ ዱ ኖርድ ጣቢያ ሐዲድ አቅራቢያ የሁለተኛ የዓለም ጦርነት ቦምብ በመገኘቱ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተሳፋሪዎች ባቡር ለመሳፈር ሲጠባበቁ።

ጋር ዱ ኖር በተባለው የፓሪስ ባቡር ጣቢያ ሐዲድ አቅራቢያ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ቦምብ በመገኘቱ በማለዳ ከፍተኛ መስተጓጎል ተፈጥሯል።

የፈረንሣይ ብሔራዊ የባቡር ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ ያልፈነዳው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ቦምብ መገኘቱ፣ የፓሪስ ከተማን፣ የሀገሪቱን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የባቡር እንቅስቃሴን አስተጓጉሏል።

“ያልፈነዳው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ቦምብ በሐዲዱ አቅራቢያ ተገኝቷል” ሲል ኩባንያው ሲያስታውቅ፣ የአሶስዬትድ ፕረስ በበኩሉ 500 የባቡር ጉዞዎች ሲሰረዙ፣ 600ሺሕ ተጓዦች መስተጓጎላቸውን የትራንስፖርት ምኒስትሩን ፊሊፔ ታባሮትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ያልፈነዳው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ቦምብ ከተወገደ በኋላ መንገዶች እንደሚከፈቱና የባቡር መሥመሮችም ክፍት እንደሚኾኑ ምኒስትሩ ጨምረው አስታውቀዋል።

ክስተቱ ፈረንሣይን ከለንደን እና ከብራስልስ ጋራ የሚያገናኙ ፈጣን ባቦሮችን ጉዞም አስተጓጉሏል። ዩሮስታር የተሰኘው የፈጣን ባቡሮ ኩባንያ ነገ ቅዳሜ ሁለት ተጨማሪ ባቡሮችን በለንደን እና ፓሪስ በመመደብ ሥራውን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የፓሪስ ፖሊስ ወደ ከተማዋ የሚያስገባ አንድ አውራ ጎዳናንና ሌላ የቀለበት መንገድ በመዝጋቱ፣ ማለዳ ወደ ሥራ የሚሄዱ ሰዎች ተስተጓጉለዋል። አውራ ጉዳናው ከሰዓታት በኋላ ክፍት ሆኗል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG