በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፀረ-አይሲል ሰልፍ ባዲሳባ


ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች
ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች

please wait

No media source currently available

0:00 0:42:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከሠልፈኞች መካከል የተጎዱና የታሠሩ አሉ፤ ለተፈጠረው ሁከት ሰማያዊ ፓርቲን በተጠያቂነት የከሰሱት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ሰባት የፖሊስ ባልደረቦች መጎዳታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ውንጀላውን አስተባብሎ የነገ ጠርቶታል ተብሎ የተነገረን ሰልፍም በሚመለከት የሚያውቀው ነገር እንደሌለም፤ ሰልፍ እንዳልጠራም ለቪኦኤ አስታውቋል፡፡

እሥላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው የሽብር ቡድንም ሆነ አል-ሻባብን የመሳሰሉ ዓለምአቀፍና አረመኔያዊ አሸባሪ ንቅናቄዎችን ለመግታት በሚካሄደው ጥረት ኢትዮጵያ አቅሟ በሚፈቅደው ደረጃ ሁሉ እንደምትሰለፍ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናግረዋል።

ኀዘን
ኀዘን

መንግሥት ሽብርተኛነትን ለማውገዝ መስቀል አደባባይ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና የሃይማኖት መሪዎቹ ያደርጉ የነበረውን ንግግር አብዛኛው ሕዝብ በፅሞና ሲያዳምጥ በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል በተለያዩ ማዕዘናት ደግሞ ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ ይሰማ ነበር።

የሠልፉ ሥነ-ሥርዓት ማብቂያ ሲቃረብ ጀምሮ በፖሊስና በመንግሥቱ ላይ ተቃውሞ ያሰሙ በነበሩ ሠልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል፡፡

የጧፍ መብራት በአይሲል ለተገደሉ ኢትዮጵያዊያን
የጧፍ መብራት በአይሲል ለተገደሉ ኢትዮጵያዊያን

በዚሁ በዛሬው የአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ የተገኙ አይሲል በኢትዮጵያዊያን ላይ ስለፈፀመው ግድያ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሊብያ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ዛሬ ከቪኦኤ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ለዝርዝር ዘገባዎች የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG