ከአብን ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር የነበሩ ሰዎች እየተለቀቁ ነው
ለረቡዕ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ ያረጋገጡት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አሁን ግን እየተለቀቁ ነው ብለዋል። ሰልፍ በተጠራበት ቀን እንወጣለን ያሉ ጥቂት ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ታስረው ነበር ነው ያሉት። ሰልፉን የጠራው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የታሱሩ አባላቱ እየተፈቱ መሆኑን ጠቅሷል የተያዙት ግን በቢሮ ውስጥ እንዳሉ እንጅ ሰልፍ ወጥተው አይደለም ብሏል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሴፕቴምበር 21, 2023
የአወዛጋቢዋ አውራ ጎዳና ወይም ቆርኬ ጥቃት አጠያያቂ እንደኾነ ነው
-
ኦገስት 26, 2023
በጋሞ ዞን በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፋ
-
ኦገስት 23, 2023
በፕሪቶርያው ስምምነት ከእስር መፈታት ሲገባቸው ያልተፈቱ እስረኞች እንዳሉ ተገለጸ