የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመን ላይ ተይዞ ለኢትዮጵያ መሰጠት በስፋት እያነጋገረ ነው፡፡
የሚመሩት ንቅናቄ ግንቦት ሰባት ተከታታይ መግለጫዎችን አውጥቷል፤ ዜጋ የሆኑበት የእንግሊዝ መንግሥት፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዋች፣ የግንቦት ሰባት አጋሮችና ሌሎችም ድርጅቶች የየመንን አድራጎት አውግዘዋል፤ የየራሣቸውን ጥያቄዎች አሰምተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥትም ሽብርተኛ መሪ መያዙንና በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የሚገባውን እንደሚያገኝ ገልጿል፡፡
ከላይ የሚገኘው የድምፅ ፋይል የእስካሁኑን ሂደቶች ማጠቃለያ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ባለቤት ወ/ሮ የምሥራች ኃይለማርያም እና የወንድማቸውን የአቶ ብዙነህ ፅጌን ሃሣቦች እንዲሁም የተለያዩ ወገኖችን አስተያየቶችና የኢትዮጵያን መንግሥት ምላሽ ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡
አቶ ሺመልስ ለራዲዮ ፍራንስ አንተርናሲዮናል በሰጡት መግለጫ ላይ የተጠናቀረውን ዘገባና ቃለ-ምልልሣቸውን ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
ግንቦት ሰባት የፍትሕ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄን መግለጫዎች ለማንበብ ከታች የተቀመጠውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
http://www.ginbot7.org/2014/07/10/ፋሽስታዊ-ፕሮፖጋንዳው-እና-ምላሻችን!/
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ የሚናገረውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናና የአቶ አንዳርጋቸውን ቃል ለማየት ከታች የተቀመጠውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
http://www.youtube.com/watch?v=LkxKkd1kk8g