በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ብዙአየሁ ፉሮ ከኢትዮጵያ ተባረሩ


አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሣልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ የአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፉሮ ከኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲወጡ መደረጉት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሣልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ የአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፉሮ ከኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲወጡ መደረጉት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ ብዙአየሁ የወንድማቸውን የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ለአሥር ቀናት ከቆዩ በኋላ ወደ ኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ተጠርተው ወዲያው ሃገር ለቅቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ወንድማቸው የሚገኙበትን ለማወቅ እንዲረዷቸው ወደ እንግሊዝ ኤምባሲና ወደ ዓለምአቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መሄዳቸን፣ እንዲሁም ምናልባት አቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት ቢቀርቡ በሚል አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ባሳሰባቸው መሠረት ጠበቃ ለመቅጠር ወዲያ ወዲህ ይሉ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

እዚያ በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ስለኢትዮጵያ መንግሥትም ይሁን ስለሌላ ማንምና ስለምንም ሁኔታ የነቀፌታም ይሁን የድጋፍ ቃል አለመናገራቸውን፣ ያደረጉት አንዳችም የሚያስባርር አድራጎት እንደሌለም ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ ወ/ሮ ብዙአየሁ ፉሮ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG