ከሰሞኑም፣ የገንዘብ ሚኒስትሩን አሕመድ ሽዴን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በብድር እና በኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ጋራ ተነጋግረዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የፋይናንስ ባለሞያ አቶ አብዱልቃድር ኑረዲን፣ በገንዘብ ድርጅቱ የተቀመጡትን አብዛኞቹን ቅድመ ኹኔታዎች ኢትዮጵያ መፈጸሟን ገልጸዋል፡፡ የቀረው ቅድመ ኹኔታ፣ የብርን የመግዛት ዐቅም ማዳከም ብቻ ነው፤ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ/ኢዜማ/ ፓርቲ፣ የብርን የመግዛት ዐቅም ማዳከም አስመልክቶ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፣ በውጭ ድርጅቶች ተጽእኖ ምክንያት ብርን የማዳከም ርምጃን እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ::