በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ቃላት በቂ አይደሉም ...” አና ጎምሽ


አና ጎመሽ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል
አና ጎመሽ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሃገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ድፍረት ይኖራቸዋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ አና ጎምሽ አስታውቀዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሃገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ድፍረት ይኖራቸዋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ አና ጎምሽ አስታውቀዋል።

ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ አንስቶ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በንቃት እየተከታተሉ የሚገኙት የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲና የአውሮፓ ሶሻሊስት ፓርቲ አባል፤ እንዲሁም የአውሮፓ ፓርላማና የፓርላማው የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል አና ማሪያ ሮሳ ጎምሽ የዶ/ር አብይ አሕመድ መሾም “ለኢትዮጵያም ሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ በጎውን ሊያመጣ፣ ጥቅማቸውን ሊያስጠብቅ የሚችል ነው” የሚል ሃሣብ በብዙዎች ዘንድ እየተንፀባረቀ መሆኑን ማስተዋላቸውን ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ጥሩ ምልክት ነው፤ ነገር ግን እስኪ ተግባሩን እንጠብቅ፤ ያ ተግባር ሰዉ የሚፈልገውን፣ የሚጠብቀውን ያሟላል፤ ይፈፅማል የሚል ተስፋ አለኝ” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ለለውጥ፣ ሁሉን አሣታፊ ለሆነ ንግግር፣ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሽግግር የሚደረግን ጥረት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደግፈውን ያህል የአውሮፓ ፓርላማና የአውሮፓ ተቋማትም ያለጥርጥር እንደሚደግፏቸው በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ” ሲሉ አክለዋል ሚስ አና ጎምሽ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ቃላት በቂ አይደሉም ...” አና ጎምሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG