በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔልሰን ማንዴላ ንብረቶች በጨረታ እንዳይሸጡ ታገደ


የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ

በጨረታ ሊሸጡ ታቅደው የነበሩ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ንብረት የሆኑ በርካታ ቅርሶች ሙሉ ለሙሉ እንዳይሸጡ እግድ የተጣለባቸው መሆኑን የደቡብ አፍሪካን የባህል ቅርስ የሚከላከለው አካል ትናንት ማክሰኞ አስታውቋል፡፡

እኤአ የካቲት 24 ሊካሄድ የታሰበው ጨረታ የተዘጋጀው ኒው ዮርክ በሚገኘው ገርንዚ በተባለው አጫራች ድርጅት እና በፕሬዚዳንት ማንዴላ የበኩር ልጅ ዶ/ር መካዝዌ ማንዴላ አማካይነት ነው፡፡

የደቡብ አፍሪካ የጸረ አፓርታይድ ትግል ቀንዲል እና በደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በዴሞክራሲያ ምርጫ የተመረጡት ፕሬዚዳንት ማንዴላ ያረፉት እኤአ በ2013 ነበር፡፡

ሽያጩ እንዲካሄድ ቀደም ሲል የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም በደቡብ አፍሪካ የቅርስ ሀብት ተከላካይ ተቋም ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ የሽያጩ እቅድ ከደቡብ አፍሪካ ህዝብና መንግሥትም ከፍተኛ ተቃውሞና ትችት ቀርቦበታል፡፡

ለጨረታው ከቀረቡት ዝርዝሮች መካከል የማንዴላ ታዋቂው ሬይ-ባን የፀሐይ መነፅር እና “ማዲባ” ሸሚዞች፣ ከእስር ቤት ሆነው የጻፏቸው የግል ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል የተበረከቱላቸው ብርድ ልብስ ይገኙበታል።

በተጨማሪም ከቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ስጦታ የተሰጣቸው የሻምፓኝ ማቀዝቀዣ በ24,000 ዶላር ለሽያጭ ከቀረቡት መካከል የሚገኝ ሲሆን ፣ የማንዴላ "መፅሃፍ" እንዲሁም - እኤአ በ1993 ከእስር እንደተፈቱ የነበራቸው የመታወቂያ ካርድ የመሳሰሉት በጨረታው ዝርዝር ውስጥ ይገኙበታል፡፡

ጨረታውን "አስገራሚ እና አስደናቂ" ስል በድህረገፁ ላይ የገልጸው አጫራቹ ተቋም ገረንዚ፣ ከጨረታው የሚገኘው ገቢ ማንዴላ በተቀበሩበት ጡኑ መንደር ውስጥ የማንዴላ መታሰቢያ የሚሆን የአትክልት ስፍራ ለመገንባት ይውላል ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG