ዋሽንግተን —
ቅዳሜ እና ዕሁድ በኦሮምያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ በከፈተውየእሩምታ ተኩስ እስካሁን 67 ሰዎች መገደላቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ከታማኝምንጮች ያገኘነው በማለት ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተማጋች ቡድን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
ሚቸል ካጋሪ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በምስራቅ አፍሪካ በመካከለኛው እና ታላላቅ ሃይቅ አከባቢ የመብቶችይዞታዎች ገምጋሚ ቡድን ምክትል ኃላፊ ናቸው ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡