No media source currently available
የአማራ ህዝብ ከወሰንና ማንነት ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ፣ ለዚሁ ጉዳይ ከተቋቋመ ሀገርቀፍ ኮሚሽን ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የክልሉ መንግሥት ይህንን ያስታወቀው ከወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አበላት ጋር በቅርቡ በባህርዳር ከተማ ከተደረገው ውይይት መነሻ አድርጎ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡