በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍኖተ ሰላም ላይ የአንድ ሰው ሕይወት ጠፋ፤ አንድ ቤት ተቃጠለ


የአማራ ክልል ካርታ /ምንጭ የተመድ/
የአማራ ክልል ካርታ /ምንጭ የተመድ/

በምዕራብ አማራ በፍኖተ ሰላም ከተማ ዛሬ በተፈጠረ ግጭትና የአንድ ሰው ቤት ለማቃጠል ሌሎች ሰዎች ሙከራ አደረጉ በተባለበት ወቅት ከባለቤቱ በተሰጠ ምላሽ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ቤቱ መቃጠሉን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ፍኖተ ሰላም ላይ የአንድ ሰው ሕይወት ጠፋ፤ አንድ ቤት ተቃጠለ /ዘገባ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:48 0:00
ከአቶ ለገሠ ተፈረደኝ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:58 0:00

በምዕራብ አማራ በፍኖተ ሰላም ከተማ ዛሬ በተፈጠረ ግጭትና የአንድ ሰው ቤት ለማቃጠል ሌሎች ሰዎች ሙከራ አደረጉ በተባለበት ወቅት ከባለቤቱ በተሰጠ ምላሽ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ቤቱ መቃጠሉን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በጎንደር ከተማ ትናንት የተጀመረው ሥራ የማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉና በባሕር ዳር ደግሞ በአድማ ላይ ተሣትፋችኋል የተባሉ የንግድ ድርጅቶች እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጎንደር ውስጥ ወደ አንገረብ ማረሚያ ቤት ትናንት የሄዱ የመከላከያ ሰዎች በዚያ ላሉ ሰዎቻቸው ደመወዝ ለመክፈል እንጂ በቁጥጥር ሥር ያሉትን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አመራር አባሉን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን ወደ ሌላ ሥፍራ ለመውሰድ እንዳልነበረ የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመልክተዋል፡፡

በርከት ላሉ ተጨማሪ መረጃዎች የጎንደርና የባሕር ዳር ከተሞች ነዋሪዎች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለገሠ ተፈረደኝ እና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ቃሎችና ቃለ-ምልልሶች የተካተቱባቸውን ከዚህ ጋር የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG