ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ገደል ውስጥ ገብቶ 25 ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ነው የተባለውና አደጋው የደረሰበት የዳውንት አካባቢ ነዋሪዎችና የዳውንት ወረዳ መናኻሪያ አስተባባሪ ስምሪት ባለሞያ የሟቾን ቁጥር እስከ 30 ከፍ ያደርጉታል።
አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኙት ሁለት ጤና ጣቢያዎች በአደጋው የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጤና ተቋማቱ መምጣታቸውን አረጋግጠው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 16 ሰዎች ወደ ደላንታ ሆስፒታል መላካቸውን አመልክተዋል፡፡አድማጮች ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም