በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ "ፈረስ ቤት" በተባለች ከተማ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት 37 ሲቪሎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦችና የከተማው ነዋሪዎች፣ የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ ከ30 በላይ የወረዳው አመራሮች በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ ባሏቸው የፋኖ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ ሰዎቹ የተገደሉት ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነው ብለዋል።
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ
ላለፉት ሁለት ወራት በፋኖ ቁጥጥር ሥር እንደነበሩ አንድ ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈልጉ የመንግሥት አንድ ግለሰብ ፣ ግድያው ሲፈጸም በቦታው ነበርኩ ብለዋል። አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ፣ የቅርብ ቤተሰባቸው አባል እንደተገደለባቸው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከፋኖ ታጣቂዎች መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ከፌደራልና ከክልል ባለሥልጣናትም መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም