መንግሥት “የሕግ ማስከበር ዘመቻ በሚል በጀመረው እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍ/ቤት የመቅረብ መብት እንዲከበር ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ማሳሰቢያ መስጠታቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቂም ኮሚቴ አባላት ገለፁ።
በአማራ ክልል ባለፈው ወር በተካሄደውና ሕግ የማስከበር ዘመቻ ብሎ በጠራው እንቅስቃሴ ከ 12 ሽ በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል።
የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በህግ ማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ከባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/