በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የዳኞች ከሥራ መልቀቅ ምክንያት ፍትሕ ቢሮው እና የዳኞች ማኅበሩ አልተግባቡም


በዐማራ ክልል የዳኞች ከሥራ መልቀቅ ምክንያት ፍትሕ ቢሮው እና የዳኞች ማኅበሩ አልተግባቡም
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:50 0:00

የዳኞች ያለመከሠሥ መብት በሕግ እንዲጸድቅ፣ የዐማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ጠየቀ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በክልሉ ምክር ቤት ተሠይመው የሚያስችሉ ዳኞች፣ በአስፈጻሚው አካል የሚደርስባቸው የመብቶች ጥሰት እንዳሳሰበው የገለጸው የዐማራ ክልል ዳኞች ማኅበር፣ ጥሰቱን ለማስቆም እንዲቻል፣ ዳኞች ያላቸው ያለመከሠሥ መብት በሕግ እንዲጸድቅ ጠይቋል፡፡

የማኅበሩ ሊቀ መንበር አቶ አበባው ታደሰ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፤ በክልሉ በተለይ ደግሞ በወረዳ ደረጃ የሚሠሩ 103 ፣ በአስፈጻሚው አካል ተፈጸመብን ባሏቸው የመብቶች ጥሰት፣ ሥራቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

የዐማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በበኩሉ፣ ዳኞች ሥራ የሚለቁበት ዋና ምክንያት፣ በደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ማነስ እንደኾነ ገልጿል፡፡

በቅርቡ ሥራቸውን የለቀቁ አንዳንድ ዳኛችም የክልሉን ፍትሕ ቢሮ አስተያየት በማጠናከር፣“ዋና ምክንያቱ፥ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ማነስ ነው፤” ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለዳኞች የተሻለ ዕድል በማመቻቸት ላይ እንደኾነ የፍትሕ ቢሮው አመልክቷል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG