በዐማራ ክልል የሚገኙ የኦሮሚያ ክልል የግጭት ተፈናቃዮች፣ የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁ፣ ተስፋቸውን እንዳጨለመባቸው ተናገሩ፡፡
ከተፈናቀሉበት ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በመጠለያ ጣቢያ እና ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው እንደሚኖሩ የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በሰላም ድርድሩ ተወልደው ወደ አደጉበት ቀዬ ተመልሰው ዳግም ለመቋቋም ተስፋ ሰንቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ድርድሩ ያለአንዳች ውጤት በመቋጨቱ ግን፣ ችግራቸውን እንደሚራዝመው ተናግረዋል፡፡
የዐማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ሓላፊ አቶ ወንድወሰን ለገሰ ደግሞ፣ ተፈናቃዮችን የመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ያለው፣ በሰላም ድርድሩ ላይ በመመሥረት እንዳልኾነ አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።