በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አበርገሌ ውስጥ በተከሰተው በሽታ የሕፃናት ሕይወት ማለፉን አርሶ አደሮች ገለፁ

አበርገሌ ውስጥ በተከሰተው በሽታ የሕፃናት ሕይወት ማለፉን አርሶ አደሮች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00

አበርገሌ ውስጥ በተከሰተው በሽታ የሕፃናት ሕይወት ማለፉን አርሶ አደሮች ገለፁ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ በህወሓት ቡድን ቁጥጥር ሥር ይገኛል በተባለው አበርገሌ ወረዳ 12 ቀበሌ በተለምዶ ፅላሪ ጀርገብ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ወረርሽኝ መከሰቱን በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለፁ።

በአሁኑ ወቅት በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዓለሙ ክፍሌ በሽታው ከተከሰተ አምስት ቀናት ማለፉን ገልፀዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ በወረርሽኙ ህጻናት እንደሞቱ ከአንድ ቀን በፊት ሪፖርት እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል፡፡

XS
SM
MD
LG