በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በውጊያ የተሳተፉ ‘የቀድሞ ተዋጊዎች’ ኹሉ ትጥቅ እንዲፈቱ ይደረጋል” - የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን


“በውጊያ የተሳተፉ ‘የቀድሞ ተዋጊዎች’ ኹሉ ትጥቅ እንዲፈቱ ይደረጋል” - የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00

በማንኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በተደራጀ መልኩ ውጊያ ውስጥ የተሳተፉ አካላት፣ ትጥቅ እንደሚፈቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን፣ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም እና በጦርነት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ውይይት፣ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋራ አድርጓል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፣ በማንኛውም ውጊያ ወይም ግጭት ውስጥ፣ በቡድን ተደራጅቶ እና መሣሪያ ታጥቆ ወደ ውጊያ የገባ “የቀድሞ ተዋጊ” ትጥቅ ይፈታል ብለዋል፡፡

“የቀድሞ ተዋጊ ማን ነው? ትጥቅ ለማስፈታት የሚያስችል መተማመን አለ ወይ? በትግራይ ክልልስ ያሉ ታጣቂዎች ገና መች ትጥቅ ፈቱ?” በሚል ለተነሣላቸው ጥያቄም ኮሚሽነሩ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር በበኩላቸው፣ በክልሉ ሰላምን በማስፈን ልማት ላይ ትኩረት እንዲደረግ ጥረታችንን እንቀጥላለን፤ ብለዋል፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG