No media source currently available
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አካባቢ ሰላም ለማስከበር የሚንቀሳቀሰውን ልዩ ኃይል አካባቢውን ለቆ ይውጣ የሚለው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የቅማንት ተወላጅ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው እንዲወጣ የጠየቅነው በልዩ ሀይል ስም ተደራጅቶ የመጣውን ፋኖ በመባል የሚንቀሳቀሰውን ሀይል ነው ብለዋል።