በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በመቀጠሉ፣ የተወሰኑ የንግድ ቤቶች መዘጋታቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት ፣ በክልሉ ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ቀራኒዮ ከተማ እና በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ ነዋሪዎች፣ ጋብ ብሎ የቆየው የተኩስ ልውውጥ እሁድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በድጋሚ በመቀጠሉ ዛሬ ድረስ አካባቢው እንዳልተረጋጋ ተናግረዋል። ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ነዋሪዎች፣ ግጭቱን ተከትሎም ዛሬ የንግድ ድርጅቶች መዘጋታቸውንና የትራንስፖር እንቅስቃሴ መታጎሉን ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ከክልሉ መንግሥት እና ከአካባቢው ባለሥልጣናት ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
መድረክ / ፎረም