በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አናዋጣም’ ስላሉ ታሠሩ”?


“አናዋጣም’ ስላሉ ታሠሩ”?
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ “ይነሳ” የተባለ ቀበሌ ነዋሪዎች “ለአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) መዋጮ እንድንከፍል እየተገደድን ነው” ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።

ቅሬታቸውን ለክልሉ መንግሥት ለማቅረብ ከተመረጡ 12 ሰዎች መካከል ሁለቱ መታሰራቸውንም ተናግረዋል።

‘አናዋጣም’ ያሉት ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በሰበሰበው መዋጮ ‘እሠራዋለሁ’ ያለውን ልማት ባለመሥራቱ እንደሆነ ገልፀው “አሁን የተጠየቅነውም ከቀድሞው የተጋነነ ነው” ብለዋል።

የዞኑ የአልማ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንቴ ታደሰ በግለሰቦቹ ላይ ‘ተፈፀመ’ የተባለው ድርጊት ከማኅበሩ ዓላማና ደንብ ውጪ መሆኑን ተናግረው ክሡ ትክክል ስለመሆን አለመሆኑ ወደ ሥፍራው ሄደው እንደሚያጣሩ አመልክተዋል።

የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ስለሚባለው አቤቱታ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ ዘገባውን የያዘውን ፋይል ይመልከቱ።

XS
SM
MD
LG