ግጭት ከነበረባቸው የኦሮምያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎች ተፈናቅለው ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። በመጠለያ እጦት በየሰዉ ቤት ተጠግተው ወይም በየጎዳናው ላይ ተበትነው እንደሚገኙና በዝናብና በብርድ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልፀዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ችግሩ መኖሩን አምነው ከኦሮምያ የተፈናቀሉትን አስመልክቶ በክልሉ 13 ሰላማዊ ወረዳዎች ውስጥ ለማስፈር ዝግጅቱ መጠናቀቁን አመልክተዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ።