ሩሲያ፣ ባለፈው ሳምንት፣ ለዚምባቡዌ በሀገሯ የተሠሩ ሄሊኮፕተሮችን ለግሳለች፡፡ ባለሥልጣናቱ፣ የሄሊኮፕተሮቹ ስጦታ፥ ሁለቱ ሀገራት፣ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የያዙት ጥረት አካል እንደኾነ ይናገራሉ፡፡
ተንታኞች በበኩላቸው፣ የሄሊኮፕተሩ ርዳታ፥ ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት እንድትገለል ጥረት እያደረጉ ካሉት ሀገራት ጎን ዚምባቡዌ ስላልተሰለፈች፣ ውለታ መክፈሏ ነው፤ ብለዋል፡፡
ኪት ባፕቲስት ከሐራሬ ዘግቦበታል፡፡ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።