በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የሚገቱ የፀረ ኮቪድ ክትባቶች ዝግጅት ጥሪ


የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የሚገቱ የፀረ ኮቪድ ክትባቶች ዝግጅት ጥሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00

የዓለም ጤና ድርጅት፣ በየጊዜው እየተለዋወጡ በአዲስ መልክ የሚከሠቱ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎችን ሊቋቋሙ የሚችሉ ዐዲስ ክትባቶች ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረበ፡፡

የመላው ዓለም ትኩረት በዝንጀሮ ፈንጣጣ ላይ ባረፈበት በዚኽ ወቅት፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኀኖም፣ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ገና ያላበቃ መኾኑን በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡ ወረርሽኙን ለመግታት፣ በውጤታማነታቸው የታወቁ የሕዝብ ጤና አጠበባቅ ርምጃዎችን ማስፋፋት እና ማጠናከር ያስፈልጋል፤ ብለዋል፡፡

ሕይወትን ለማዳን እጅግ ውጤታማ ከኾኑ ርምጃዎች መካከል አንዱ፣ ክትባትን በቅድሚያ ለትክከለኛው የማኅበረሰብ ክፍል ማድረስ ነው፤ ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ የኮቪድ-19 ተጋላጮች እና ሟቾች ቁጥር፣ ባላፉት አምስት ሳምንታት ውስጥ መጨመሩንም ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡

በቅርቡ የወጣው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት፣ በዓለም በበሽታው የሞቱትን 6.3 ሚሊዮን ሰዎች ጨምሮ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ወደ 566 ሚሊዮን መዳረሱን አመልክቷል፡፡ በኦሚክሮን ዝርያ ሳቢያ በፍጥነት እየተላለፈ የሚገኘው ቫይረሱ፣ በበርካታ አገሮች ወደ ሆስፒታል የገቡ ሕሙማንን ቁጥር እንደጨመረ ተናግረዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG