በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ካንሰርን ለማከም የሚጠቅሙ የቫይረስ ዝርያዎች አሉ” - ዶ/ር ዘላለም ኃይሉ


“ካንሰርን ለማከም የሚጠቅሙ የቫይረስ ዝርያዎች አሉ” - ዶ/ር ዘላለም ኃይሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00

ለልዩ ልዩ በሽታዎች መንሥኤነት ወይም በወረርሽኝ ቀስቃሽነት የሚታወቁት “ቫይረስ” የተሰኙ ረቂቅ ተዋሕስያን፣ በሽታዎችንና ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚያስችል ጥቅም እንዲኖራቸው ተደርገው ሊሠሩ እንደሚችሉ፣ አንድ ባለሞያ ተናገሩ።

በዩናይትድ ስቴትሱ ኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ፕሮግራም የረቂቅ ሕዋሳት ምርምር ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዶር. ዘላለም ኃይሉ መኩሪያ፣ ቫይረሶች፥ በሰውም ኾነ በእንስሳት ላይ ጉዳት አማጭ ብቻ ተደርገው እንደሚታሰቡ ገልጸው፣ አሁን ግን የቫይረሶችን አስፈላጊነት እና ጥቅም የማገናዘብ ደረጃ ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

“ወደ 25 የሚኾኑ የቫይረስ ቤተሰቦች አሉ፡፡ አብዛኞቹ፣ በሰውም ኾነ በእንስሳት ላይ ምንም ዐይነት ጉዳት አያመጡም፤” ያሉት ዶር. ዘላለም፣ “የምናውቀውን ዓይነት ወረርሽኝ ወይም በሽታ የሚያመጡት ጥቂቶቹ ናቸው፤” ብለዋል።

በአኹኑ ሰዓት፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ ታላላቅ ሆስፒታሎች፣ ካንሰርን ሊከላከል የሚችል፣ ከቫይረስ የተሠራ የፈውስ ዐይነት ስለመኖሩም ባለሞያው ጠቁመዋል። “የካንሰር ሕዋሳትን ብቻ ለይቶ እና ለቅሞ እንዲያጠፋ የሚያደርግ የፈውስ ዐይነት ነው፤” ያሉት ዶር. ዘላለም፣ በአሁኑ ሰዓት፣ መድኃኒቶቹ በጥናት ደረጃ ላይ እንዳሉና ለሕክምና አገልግሎት እንዳልዋሉ ገልጸዋል።

በሳምንታዊው “ሐኪሞን ይጠይቁ” ቅንብር ላይ ቀርበው፣ ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን፣ ዶር. ዘላለም ኃይሉ መኩሪያ፣ ቫይረሶች፥ “በሽታ አምጪ ወይስ የሕክምና መሣሪያ? ወይስ ሁለቱንም?” ለሚሉ ጥያቄች ማብራሪያዎችን ሰጥተውናል።

XS
SM
MD
LG