አዲሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዚህ ሳምንት ባደረጉት ያልተለመደ ቀጥተኛና ‘ጠብ ጠብ የሚሸትት’ የተባለ ንግግር የቤጂንግ ባለሥልጣናት በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የነቅፌታ ውርጅብኝ አሳርፈዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ቻይናን አላፈናፍን በማለቷ ከቀጠለች የሚፈጠረው መፋጠጥ ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ሚኒስትሩ ቺን ጋንግ አስጠንቅቀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ቻይናን ‘ካለችበት እንዳትወጣ ወይም እንዳትንሠራፋ ሰቅዞ የመያዝ ፍላጎት እንደሌላት’ ገልፃ ግንኙነታቸውን በተመለከተም ‘የተቀየረ ምንም ነገር የለም’ ብላለች።