በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግራይ ክልል የሚገባው እርዳታ እንዲጨምር እየሠራ መሆኑን ተመድ አስታወቀ


ትግራይ ክልል የሚገባው እርዳታ እንዲጨምር እየሠራ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

ለአማራ ክልል እርዳታ ፈላጊዎች በሚቀርበው ላይ ለውጥ እንደሌለው ክልሉ ገልጿል

ከሰላም ሥምምነቱ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የዕርዳታ አቅርቦት መጠን እንዲጨምር ማስተባበር በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ ዓመት ካከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሚጠቀስ ተመድ ገለጸ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ቢሮው ባወጣው የግምገማ ሪፖርት በ2022 ዓ.ም በሰሜን ኢትዮጵያ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተለያየ ድጋፍ ደርሷቸዋል ብሏል፡፡

ድርጅቱ ከሰላም ሥምምነቱ በኋላ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ ለተጎዱ ክልሎች የሚደርሰው የድጋፍ አቅርቦት እየጨመረ መሆኑን ቢገልጽም፣ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ በክልሉ በሚቀርበው የድጋፍ መጠን ላይ ለውጥ እንደሌለ አመልክቷል፡፡

በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ተወካይ ዳይሬክተር ጌቴ ምህረቴ ችግሩን ለመቅረፍ ከለጋሾች ጋራ ንግግር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያይዘው የምስል ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG