በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሶማሊያውያን ስደተኞች ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተጠየቀ


በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሶማሊያውያን ስደተኞች ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00

በሶማሌላንድ ሠራዊት አባላትና በታጣቂዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሶማሌያዊያን ስደተኞች ቁጥር 83 ሺህ መድረሱን የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋራ ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል።

ስደተኞቹ ለአደጋ የተጋለጡ በመሆናቸው ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እርዳታ እንዲያደርግላቸው በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የኮምዩኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ በአካል ንጉሴ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ስደተኞች ውስጥ እስካሁን እርዳታ ማግኘት የቻሉት ሁለት ሺህ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም አቶ በአካል ገልፀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG