በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠለምት ውስጥ የምግብ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገለፁ


ጠለምት ውስጥ የምግብ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:21 0:00

በጠለምትና በዙሪያው ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በመቶ ሺሆች የሚቆጠር ሰው በከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ መሆናቸውን ከአካባቢው የወጡ ሰዎችና የማንነት ጥያቄን መሠረት አድርጎ የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቀዋል።

በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ ሃለፎም ረዳኢ በበኩላቸው ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ እንደማይገባና አለ የሚሉት የነዳጅ እጥረት የገባውንም ለተረጂዎች እንዳያደርሱ ያደረጋቸው መሆኑን አመልክተዋል።

በጉዳዩ ላይ ሰሞኑን ከዓለምአቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር መነጋገሩን ያመለከተው የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን በቅርብ ቀን እርዳታ እንደሚጓጓዝ ተስፋውን ገልጿል።

እንደወልቃይትና ራያ ሁሉ ጠለምትና አካባቢው በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የማንነትና የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ሲነሳበት የቆየ መሆኑንም ይሄንኑ መነሻ አድርጎ የተቋቋመ ኮሚቴ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG