በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የሱዳን ግጭት የሟቾች ቁጥር ከ300 በላይ አሻቀበ


ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የሱዳን ግጭት የሟቾች ቁጥር ከ300 በላይ አሻቀበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል፣ ለሁለተኛ ጊዜ ታስቦ የከሸፈውን የ24 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ ውጊያው ለስድስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።

በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ልዩ ኃይሉ መካከል በቀጠለው ግጭት፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 300 መድረሱንና ከሦስት ሺሕ በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጤና ተቋም አስታውቋል፡፡

ኾኖም የሟቾች ቁጥር፣ በተቋሙ ከተገለጸውም በላይ ሊኾን እንደሚችል ተጠቁሟል።

በተያያዘ ዜና፣ ከሱዳን ጦር ጋራ፣ “የአየር ኃይል ልምምድ” ለማድረግ በሚል የገቡ ግብጻውያንን ማስወጣት መቻሉን፣ የሱዳን ጦር ሰራዊት ይፋ አድርጓል።

በሌላ በኩል፣ 320 የሱዳን ተጠባባቂ ወታደሮች ለቻድ እጅ መስጠታቸውን፣ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል፡፡ የሱዳናውያን ፍልሰተኞች ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሚል ስጋት ድንበሩን መዝጋቱንም ገልጿል፡፡

ከልዩ ልዩ የዜና ምንጮች የተሰበሰበውንና ወቅታዊውን የሱዳን ኹኔታ የሚዳስሰውን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ አሰናድታዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG