የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን 300, 000 ወታደሮችን የማንቀሳቀስ እቅድ የድክመት ምልክት ሲሆን ሞስኮ እየተንገታገተች መሆኗን የሚያሳይ ነው” ሲሉ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡
ተንታኞች እንደሚሉት ፑቲን ተጠባባቂ ጦሯቸውን መጥራታቸው ሰባት ወራት ላስቆጠረውን ሩሲያ በዩክሬን ያደረገችውን ወረራ አስመልክቶ በአገር ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ሊያጠናክርባቸው ይችላል። “እርምጃው በጦር ሜዳው ለሩሲያ የሚያመጣ ውጤታማነት ስለመኖሩ ግን እርግጠኛ አይደለም” ይላሉ።