በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህወሓት ከሽብር መዝገብ መፋቅና ፓርላማው


የህወሓት ከሽብር መዝገብ መፋቅና ፓርላማው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

“የሰላም ሥምምነቱን ሳይተገብር ህወሓትን ከሽብርተኛነት መሠረዝ ዳግም የሀገር ሥጋት የሚሆንበትን ዕድል እንደመስጠት ይቆጠራል” ሲል ኢዜማ ተቃውሞ አሰምቷል።

የኢዜማ ምክትል መሪ ዮሐንስ መኮንን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት “ሊከሰት ለሚችል ችግር ገዥው ፓርቲና መንግሥት ኃላፊነት ይወስዳሉ” ብለዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄም ውሳኔውን ተቃውሟል።

ትናንት፤ ረቡዕ በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይም እንዲሁ የተቃውሞ ድምፆች ተሰምተዋል።

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የተገኙት ከፕሪቶርያ የመንግሥት ተደራዳሪዎችና ፈራሚዎች አንዱ የሆኑት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በሰጡት ምላሽ ህወሓትን ከሽብር መዝገብ መሠረዝ የሰላም ሥምምነቱ አካል መሆኑንና ህወሓትም ለዚህ የሚያበቃውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አብራርተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።

XS
SM
MD
LG