በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ የኮሌራ ወረርሽኝ እየተዛመተ ነው


በኦሮሚያ የኮሌራ ወረርሽኝ እየተዛመተ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

· 3ነጥብ 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ወረርሽኙ ያሰጋቸዋል

· ኦቻ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አስቸኳይ ድጋፍ ጠይቋል

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባባሪያ ቢሮ(ኦቻ)፣ በኦሮሚያ ክልል በአምስት ዞኖች የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ መከሠቱን አስታወቀ።ኦቻ ሰሞኑን በአወጣው መግለጫ፣ በክልሉ፥ ምሥራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፣ 50 ሰዎች በወረርሽኙ መሞታቸውን ጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ 3ነጥብ3 ሚልዮን ዜጎች፣ በኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ መኾናቸን የጠቀሰው ኦቻ፣

በመዛመት ላይ ለሚገኘው ወረርሽኝ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አስቸኳይ ድጋፍ ጠይቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በበኩሉ፣ የኮሌራ በሽታ፣ በአምስት ዞኖች በወረርሽኝ ደረጃ መከሠቱን አረጋግጧል፡፡

የጉጂ እና የምሥራቅ ባሌ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በሽታው በፍጥነት በመስፋፋት ላይ እንዳለ ገልጸው፣ አፋጣኝ

የሕክምና አገልግሎት እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG