በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነቱ የተፈናቃይ ቁጥር እያንሰራራ ነው


በጦርነቱ የተፈናቃይ ቁጥር እያንሰራራ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00

ሰሞኑን እንደገና በተጀመረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከቆቦና ከአካባቢው ወደ 150 ሺህ ሰው መፈናቀሉን የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

በየቦታው ተበታትነው ያሉ ተፈናቃዮችን መርሳ ላይ በየትምህርት ቤቱ እያሰባሰበ መሆኑን የገለፀው የዞኑ አስተዳዳር የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ግን ማቅረብ እንዳልቻለ አመልክቷል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮችም በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ባለፈው መጋቢት ከመቆሙ በፊት በነበረው ጦርነት ከተፈናቀሉት ወደ አንድ ሚሊየን ተኩል ከሚሆኑት አብዛኞዎቹ ወደየቀያቸው ተመልሰው እንደነበር ያስታወሰው የአማራ ክልል መንግሥት ደግሞ አሁን ያገረሸው ጦርነት የተፈናቃዮቹን ቁጥር እንደገና እንዲያንሠራራ እንዳደረገው ጠቁሟል።

አፋር ክልልም እንዲሁ በጦርነቱ ከ200 ሺህ በላይ ሰው እንደተፈናቀለበት ገልጿል።

በሌላ በኩል ካለፈው ሣምንት ወልዲያ ውስጥ ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG