በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ይፋ በሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ዓመታዊ ሪፖርት “24 ሀገራት ማዕቀብ ሊጣልባቸው ይችላል”


ይፋ በሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ዓመታዊ ሪፖርት “24 ሀገራት ማዕቀብ ሊጣልባቸው ይችላል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:41 0:00

በዓለም ዙሪያ፣ ባለፈው ዓመት የታየውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን አስመልክቶ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ ዓመታዊ ሪፖርቱን አውጥቷል። ዓመታዊው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሪፖርት፣ 24 ሀገራትን፣ በአደገኛ እና አሳሳቢ ብሎ በሚጠራው ምድብ-3 ውስጥ አካቷቸዋል።

ከእነርሱም ውስጥ፥ አፍጋኒስታን፣ በርማ፣ ካምቦዲያ፣ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሩሲያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቬንዝዌላ ይገኙበታል። ሪፖርቱ በምድብ - 3 ውስጥ የሚገኙት ሀገራቱ፣ የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ መመዘኛ ያላሟሉና መመዘኛውን ለሟሟላትም በቂ ጥረት ሲያደርጉ ያልታዩ ናቸው፤ ብሏል። በመኾኑም፣ ማዕቀብ ሊጣልባቸው ይችላል። ሪፖርቱ በተጨማሪም፣ ሊቢያን፣ ሶማሊያንና የመንን በልዩ ምድብ አይቷቸዋል። በየሀገራቱ እየተካሔደ ያለው የእርስ በርስ ግጭት፣ መረጃን ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ኹኔታን ፈጥሯል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የዘንድሮው ሪፖርት፣ በርካታ አሳሳቢ አዝማሚያዎችን እንደያዘ አመልክተዋል። ከእኒኽም፣ የአዳጊ እና እንቡጥ ወንድ ልጆች ሕገ ወጥ ዝውውር መጨመር፣ የግዳጅ ሥራ መስፋፋት፣ እንዲሁም በበይነ መረብ አማካይነት ሠራተኞችን ወደ ሌላ አገር በሕገ ወጥ መንገድ ማሸጋገር የሚሉት በዋናነት ተዘርዝረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ፣ አሳሳቢውን አዝማሚያ በእጅጉ እንዳባባሰው የጠቀሱት ብሊንከን፣ ከፍተኛ የሥራ ዐጦች ቁጥር መኖርም፣ ለሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማማለያ ምቹ ኹኔታ እንደፈጠረ አስረድተዋል። “ሰለባዎቹን፣ በሐሰተኛ የሥራ ማስታወቂያ በማማለል ከወሰዷቸው በኋላ፣ ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን እንዲፈጽሙ ያደርጓቸዋል፤” ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፡፡

ብሊንከን አያይዘው በዓመቱ ስለታዩ መሻሻሎችም ሲናገሩ፣ በመላው ዓለም በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት፣ ሰለባዎቹን ለመከባከብ፣ እንዲሁም ወንጀል ፈጻሚዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG