በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ ፍ/ቤት 38 ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በዕድሜ ልክ እስራት ቀጣ


የሊቢያ ፍ/ቤት 38 ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በዕድሜ ልክ እስራት ቀጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:56 0:00

በሊቢያ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኝ ፍርድ ቤት፣ በፍልሰተኞች ሞት እና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የከሠሣቸውን 38 ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ወሰነባቸው፡፡

ከእነርሱም መካከል፣ የሜዲትሬኒያንን ባሕር በመናኛ ጀልባ በማቋረጥ፣ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሲሞክሩ፣ ሕይወታቸው ባለፈው 11 ፍልሰተኞች ሞት እና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተከሠሡት አምስቱ ሰዎች ደግሞ፣ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው፣ የአገሪቱ ዋና ዐቃቤ ሕግ ቢሮ፣ ትላንት ሰኞ አስታውቋል።

ሊቢያ ውስጥ በባይዳ ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት፣ ሌሎች ዘጠኝ ተከሳሾችም፣ እያንዳንዳቸው በ15 ዓመት እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን፣ የዋና ዐቃቤ ህጉ፣ አስ አል ሰዲቅ አል ሱር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ሌሎች 24 ሰዎች ደግሞ የአንድ ዓመት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑን ጽ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ተከሳሾቹ፣ ፍልስተኞቹ ከሊቢያ ወደ አውሮፓ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የሚተላለፉበት መረብ ተሳታፊ አካል መሆናቸውን መግለጫው ገልጿል፡፡

የአሶሺዬትድ ፕሬስን ዘገባ ነው ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG