‘ኬንያ ክዋንዛ አላያንስ’ በሚባለው የ12 የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ሩቶ ፕሬዚዳንትነታቸው ለሁሉም ኬንያዊያን መሆኑን ተናግረዋል።
ሩቶ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ተወዳዳሪያቸው የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱ ባሳወቁ ማግስት ነው።
ክሡን እንደሚከላከሉ ያሳወቁት በነባሩ የኬንያታ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው እያገለገሉ ያሉት ሩቶ አዲሶቹ ተመራጭ መሪዎች ለህዝቡ እንዲሠሩ አሳስበዋል።