የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በኢትዮጵያ አሳሳቢ የኅብረተሰብ ጤና ስጋት መኾኑ እንዳበቃ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የዓለም ጤና ድርጅትን ምክረ ሐሳብ ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት፣ የዓለማችን ቀዳሚ የጤና ጠንቅ ኾኖ አእላፋትን ለኅልፈተ ሕይወት የዳረገው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ የኅብረተሰብ ጤና ስጋት መኾኑ እንዳበቃ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ከሦስት ቀናት በፊት አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያም ይህን የድርጅቱን መግለጫ ተቀብላ፣ ወረርሽኙ፣ አሳሳቢ የኅብረተሰብ ጤና ስጋት መኾኑ እንዳበቃ፣ በዛሬው ዕለት በጤና ሚኒስቴር በኩል በአወጣችው መግለጫ አስታውቃለች፡፡
/ሙሉ ዘገባው ከፋይሉ ጋራ ተያይዟል/