በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖሊስ በእነረዳት ፕር. ሲሳይ አውግቼው ላይ ምርመራ ማጠናቀቁን ገለጸ


ፖሊስ በእነረዳት ፕር. ሲሳይ አውግቼው ላይ ምርመራ ማጠናቀቁን ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:23 0:00

ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቼውን ጨምሮ፣ በዐማራ ክልል ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋራ በተያያዘ፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል በስድስቱ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ ማጠናቀቁን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በግለሰቦቹ ላይ ክሥ እንዲመሠርት፣ ፍርድ ቤት ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን ጊዜ መስጠቱን፣ ከተጠርጣሪ ጠበቆች አንዱ የኾኑት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡

በረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቼው እና በዶር. ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር፣ በሽብር ወንጀል የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ትላንት ረቡዕ፣ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል፡፡

ፖሊስ፣ በሁለቱ መዝገቦች ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች መካከል፣ በስድስቱ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልጾ፣ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ያስተላለፈ ሲኾን፣ በችሎቱ ክርክር ከተደረገ በኋላ ለዐቃቤ ሕግ ክሥ መመሥረቻ የ15 ቀን ቀጠሮ እንደተሰጠው፣ ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በረዳት ፕር. ሲሳይ መዝገብ ሥር ከሚገኙ የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች መካከል የኾነው “የዐማራ ድምፅ” የተባለ ዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን አዘጋጅ ጎበዜ ሲሳይ ደግሞ፣ ከ14 ቀናት ቀጠሮ በኋላ ትላንት ለሁለተኛ ጊዜ፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ12 ቀን ተጨማሪ ቀጠሮ እንደተሰጠበት ጠበቃ ሰሎሞን አስረድተዋል፡፡

የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፣ ጎበዜን፣ ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን ነበር፣ ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ሥር አውሎ ወደ ዐዲስ አበባ እንዳመጣው ገልጾ ነበር፡፡

የቀን ሠራተኛ ነው የተባለው ሰሎሞን ልመንህ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህር እና የፒኤችዲ ተማሪ የኾነው ነዋይ ዮሐንስ፣ እንዲሁም ጆን ተሻገር የተባለ የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ደግሞ፣ በተለያየ የገንዘብ መጠን በዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG