በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ሥራቸውን በኢትዮጵያ ጉብኝት ጀምረዋል


አዲሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ሥራቸውን በኢትዮጵያ ጉብኝት ጀምረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በፌስ ቡክ ገፃቸው ስለ ውይይቱ ያጋሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፤ “ውይይታችን በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል” ብለዋል።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ ጋር በነበራቸው ቆይታ ደግሞ “ከፊል የዕዳ ስረዛ ስምምነት መፈራረማቸው” ተገልጿል፡፡

በነገው ዕለት ከአፍሪካ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብለው የሚጠበቁት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ቀጥለው አራት የአፍሪካ ሀገሮችን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ቺን ጋንግ ከሹመታቸው በኋላ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝታቸውን በአፍሪካ የጀመሩ ሲሆን ኢትዮጵያን ቀዳሚ መዳረሻቸው አድርገዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም "ይህም ቻይና ከአፍሪካ ጋር ላላት የቆየ ወዳጅነት እና ለቻይና-አፍሪካ ግንኙነት እድገት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ የሚያሳይ ነው" ማለታቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡

XS
SM
MD
LG