በሊቢያ አቅራቢያ ስደተኞችን የያዘ አንድ መርከብ ማክሰኞ ዕለት ተገልብጦ 73 ስደተኞች መጥፋታቸው እና ምናልባትም ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ዛሬ በትዊተር ገፁ አስታወቀ።
ወደ አውሮፓ ለመሻገር በጀልባ ተሳፍረው ይጓዙ የነበሩ 80 መንገደኞች በሊቢያ አቅራቢያ ሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ባጋጠማቸው የመገልበጥ አደጋ ቢያንስ 73ቱ መጥፋታቸውን እና ምናልባትም ህይወታቸው አልፎ ሊሆን እንደሚችል ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።
ከሞት የተረፉ ሰባት ሰዎች ወደ ባህር ዳርቻው መውጣት የቻሉ ሲሆን ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በስተምስራቅ ከሚገኘው ቃስር አልካያር የተባለ ሥፍራ መነሳታቸውን እና ወደ አውሮፓ እያቀኑ እንደነበር መናገራቸውን የስደተኛ ተቋሙ ጨምሮ ገልጿል።
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።