በኢትዮጵያ በጦርነት እና በግጭት ምክኒያት ጉዳት የደረሰባቸው ትምሕርት ቤቶች የመልሶ ግንባታ ሊደረግላቸው እንደሆነ ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተቋራጮችና ለአማካሪዎች የሥራ መመሪያ ለመስጠት ዛሬ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ይፋ እንዳደረገው በዚህ ዓመት የ71 ትምሕርት ቤቶች ግንባታ እንደሚካሄድ ገልጿል።
ተመድ ከአንድ ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርት መሰረት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክኒያት ከትግራይ፣ ከአፋር እና ከአማራ 2.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታቸው መስተጓጎላቸውን አስታውቆ ነበር። ዛሬ ይፋ የተደረገው ግንባታ ትግራይ ክልልን ያላካተተ ሲሆን የትምሕርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የዳሰሳ ጥናት ከተደረገ በኋላ ትግራይም በቀጣይ እንደሚካተት ተናግረዋል።