በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ጎንደር ዞን የአርሶ አደሮች ግድያ እና እገታ መባባሱ ተገለጸ


በምዕራብ ጎንደር ዞን የአርሶ አደሮች ግድያ እና እገታ መባባሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:47 0:00

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ፣ ለሱዳን ድንበር አቅራቢያ በኾኑ አንዳንድ ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች፣ በሥራ ላይ እንዳሉ በታጣቂዎች የሚገደሉ አርሶ አደሮች ቁጥር እየጨመረ እንደመጣ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሥራ ሓላፊዎች እና የክልሉ ባለሥልጣናት ገለጹ።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ፣ በወረዳው ሽንፋ እና ሽኩርያ በተባሉ ቀበሌዎች፣ በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ እና ሦስት ሰዎች ደግሞ እንደታገቱ፣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። በዚኽም ምክንያት፣ በአካባቢው የእርሻ ሥራ መቆሙንም ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው አርሶ አደሮችም፣ ግድያ እና እገታ የሚፈጽሙት፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ የጠሯቸው የቅማንት ታጣቂዎች እንደኾኑና ከዚኽ በፊት ከክልሉ መንግሥት ጋራ ዕርቀ ሰላም ፈጽመው በምሕረት ገብተው እንደነበር አውስተዋል፡፡

በዚኹ ወረዳ፣ ሳቃ በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ የቅማንት ተወላጆች እንደተናገሩት፣ በአካባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች፣ የአንድ ቤተሰብ አባላት የኾኑ ስድስት ሰዎችን አግተው የጠየቁት 600ሺሕ ብር ከተከፈለ በኋላ፣ ከአገቷቸው እና ገንዘብ ይዘው ከሔዱት ውስጥ፣ አምስት ሰዎችን እንደገደሉ ገልጸዋል።

የቅማንት የማንነት እና ራስ ገዝ አስተዳደር አስመላሽ ኮሚቴ አባል እንደኾኑ የተናገሩ አንድ ግለሰብ በአንጻሩ፣ በአካባቢው የቅማንትንም ኾነ የዐማራ ሕዝብን የማይወክሉ፣ “ሽፍታ” ሲሉ የጠሯቸው ኃይሎች፣ ንጹሐን ዜጎችን እያሠቃዩ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው፥ በአካባቢው ግድያ እና እገታ መኖሩን አምነው፣ የሚያረጋጋ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ወደ ሥፍራው ተልኳል፤ ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG